ስልጣን በቃኝ ያሉት የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በ10 ዓመት ውስጥ ስድስት ደረሱ
በዓሥር ዓመታት ውስጥ ስድስት ጠቅላይ ሚኒስትሮች፦ ዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የፖለቲካ አለመረጋጋት ያስተናገደች ሲሆን፣ በተለይም ከ2016 እስከ 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ስድስት ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከሥልጣን መነሳታቸው ተመዝግቧል።
ይህ ተከታታይ የሥልጣን ለውጥ ማዕበል የጀመረው እ.ኤ.አ. በ2016 ዴቪድ ካሜሩን የብሬክዚት (Brexit) ውሳኔን ተከትሎ ከሥልጣን በገዛ ፈቃዳቸው ሲለቁ ነበር።
እሳቸውን የተኩት ቴሬዛ ሜይ ደግሞ የብሬክዚት ስምምነታቸውን በፓርላማ ማጽደቅ ባለመቻላቸው ሳቢያ ከአሥረኛ ቁጥር ዳውኒንግ ስትሪት በ2019 ለመልቀቅ ተገደዋል።
በ2019 የሃገሪቱን መሪነት የተረከቡት ቦሪስ ጆንሰን በተለያዩ ቅሌቶችና በሚኒስትሮቻቸው የጅምላ መልቀቅ ምክንያት በ2022 ከኃላፊነታቸው ወርደዋል።
በመቀጠል የመጡት ሊዝ ትረስ ደግሞ የብሪታንያ ታሪክ አጭር የሥልጣን ዘመን ያስመዘገቡ መሪ በመሆን የተመዘገቡ ሲሆን፣ በመንግሥታቸው አነስተኛ የበጀት ማሻሻያ ሳቢያ በተቀሰቀሰው የኢኮኖሚ መናጋት ምክንያት በ49 ቀናት ውስጥ ብቻ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገድደዋል።
በዚያው ዓመት በ2022 ማጠናቀቂያ ላይ ሪሺ ሱናክ ኃላፊነቱን የወሰዱ ሲሆን፣ የሌበር ፓርቲ የ2024ን አጠቃላይ ምርጫ በሰፊ ልዩነት እስኪያሸንፍ ድረስ ሃገሪቱን መርተዋል።
ምርጫውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ኬር ስታርመር በበኩላቸው በ2026 ከሥልጣን መነሳታቸው፣ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ስድስተኛው የቅብብሎሽ ለውጥ ሆኖ እንዲመዘገብ አድርጓል።
የፖለቲካ ተንታኞች ይህንን የሃገሪቱን አስርት ዓመት እጅግ ፈታኝ ከሆኑት የታሪክ ምዕራፎች አንዱ አድርገው የሚገልጹት ሲሆን፣ ለዚህም በምክንያትነት የብሬክዚት ሂደት ያስከተለውን ቀውስ፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችን፣ የፓርቲዎች የውስጥ ክፍፍል እና የሕዝብ ፍላጎት መለዋወጥን ይጠቅሳሉ።
ከ2016 እስከ 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ ከሥልጣን የለቀቁት መሪዎች
1. ዴቪድ ካሜሩን በ2016፣
2.ቴሬዛ ሜይ በ2019፣
3. ቦሪስ ጆንሰን በ2022፣
4.ሊዝ ትረስ በ2022፣
5. ሪሺ ሱናክ በ2024 እንዲሁም
6. የገነርስ ቀንደኛ ደጋፊ ኬር ስታርመር ዛሬ ስልጣን በቃኝ ብለው ለቀዋል።
በቴሌግራም ይቀላቀሉ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://t.me/utopiatowday
Subscribe to get the latest posts sent to your email.
