23 Jun 2026, Tue

‘ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት’ መቀመጫውን አልረከብም አለ ፡ ውሳኔውን የሚጥስ ተመራጭ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ፤

ሰባተኛው አጠቃላይ የ2018 ዓ.ም. ሀገራዊ ምርጫ የተሳተፈው ‘ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት’ ጥምረት፣ ያሸነፋቸውን ወንበሮች ላለመረከብ መወሰኑን ለቢቢሲ አማርኛ አስታውቋል።

የጥምረቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌትነት ወርቁ፣ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ውሳኔው ምርጫውን ከመቀበል ይልቅ “ለመደራደሪያ መሣሪያነት” የያዙት አቋም ነው። ጥምረቱ በምርጫው ተሳተፈው ለቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች ምላሽ ይገኛል በሚል እምነት እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ መንግሥት ለሰላም፣ ለእስረኞች መፈታት እና ለፖለቲካ ምኅዳር መስተካከል ቀና ምላሽ ከሰጠ ውሳኔያቸውን ሊቀይሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

አቶ ጌትነት አክለውም፣ ጥምረቱ በምርጫው የተሳተፈው “የጨረባ” ብለው በገለጹት ሂደት ውስጥ መንግሥትን ወደ መነጋገሪያ ጠረጴዛ ለማምጣት እንደነበር ጠቁመዋል። መንግሥት እስኪደራደር ድረስ ለምርጫው እውቅና እንደማይሰጡ እና ሌሎች አገራትም እውቅና እንዳይሰጡት ውትወታ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ ውጤት መሠረት፣ ጥምረቱ በአጠቃላይ ሰባት ወንበሮችን ማሸነፍ ችሏል፦

👉ሁለት (2) መቀመጫዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

👉አምስት (5) መቀመጫዎች በተለያዩ የክልል ምክር ቤቶች

ጥምረቱ በአዲስ አበባ፣ በአማራ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በአጠቃላይ 1,032 ዕጩዎችን በማቅረብ፣ ከብልጽግና እና ከኢዜማ ቀጥሎ ሦስተኛው ከፍተኛ ተመራጮችን ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

በሌላ በኩል፣ ጥምረቱ ተመራጮቹ የፓርቲውን የጋራ አቋም እንዲያከብሩ ማሳሰቡን የገለጸ ሲሆን፤ የድርጅቱን ውሳኔ ጥሰው በግል ምክር ቤት የሚገቡ ተመራጮች ካሉ፣ ፓርቲው ባወጣው የውስጥ ደንብ እና የሥነ-ምግባር ሕግ መሠረት ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስታውቋል። አቶ ጌትነት “ማንኛውም ዕጩ ትብብርን ወክሎ ሊገባ አይችልም፤ እስከ ፓርቲ ማባረር የሚደርስ እርምጃ እንወስዳለን” በማለት የፓርቲውን ጽኑ አቋም አስረድተዋል።

በቴሌግራም ይቀላቀሉ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://t.me/utopiatowday


Discover more from ኢትዮጵያ ዛሬ ፤

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Leave a Reply

Discover more from ኢትዮጵያ ዛሬ ፤

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading